ስለ ባለቤት
ይበልጥ የተቀናጀ በሆነ መንገድ ንብረት ማስተዳደር
ባለቤት በኢትዮጵያ ያሉ ባለንብረቶችና አስተዳዳሪዎች የዕለት ተዕለት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የንብረት አስተዳደር መተግበሪያ እና የንብረት ዝርዝር ማስተዋወቅያ መድረክ ነው።
በአንድሮይድ (Android) እና ዊንዶውስ (Windows) መተግበሪያዎች የንብረት መዋቅርን፣ ተከራዮችን፣ ውሎችን፣ ክፍያዎችን እና ማስታወሻዎችን በአንድ ቦታ ያስተዳድራሉ።
አንድ ንብረት ዝግጁ ሲሆን፣ በአስተዳዳሪው የተመረጡ መረጃዎችን እና ፎቶዎችን በባለቤት (BaleBet) ድረ-ገጽ ማስተዋወቅ ይችላል። የግል አስተዳደር መዝገቦች ተለይተው (በኮምፒዩተርዎ/ስልክዎ) ይቀመጣሉ።
ፈጠራ
ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ያለማቋረጥ የምንሻሻል ነን።
ታማኝነት
መዝገቦችን በራስዎ (በኮምፒዩተር/ስልክ) ላይ ማስተዳደር እና የፈለጉትን ንብረት በባለቤት (BaleBet) ድህረ ገጽ ላይ ማስተዋወቅ
ውጤታማነት
ጊዜዎን የሚቆጥቡ የተቀላጠፉ የስራ ሂደቶች።
እንክብካቤ
ለስኬትዎ ያተኮረ ድጋፍ